ስለ ኢ.ሲ.ዲ.ዲ. የመረጃ አገልግሎት
ኢ.ሲ.ዲ.ዲ በአካል ጉዳተኝነት ዙሪያ የመረጃ አገልግሎት ማእከል በማቋቋም በኢትዮጵያ በአካል ጉዳተኝነትና በልማት ዙርያ፣ አካል ጉዳተኞችና ቤተሰቦቻቸው አስመልክቶ
ያሉ አገልግሎቶችና ፕሮግራሞች ለተጠቃሚዎች ያቀርባል፡፡ እንደዚሁም በተጨባጭ አካታች ልማትን ለማስፈን በቀዳሚነት ይሰራል፡፡
የኢ.ሲ.ዲ.ዲ መረጃ ማእከል በኢትዮጵያ
ስለ አካል ጉዳተኛ ሰዎች ሁኔታና እንዲሁም የጥናትና ምርምር ሥራዎች፣የዩኒቨርስቲ መመረቅያ ፅሁፎች፣ በተባባሩት መንግስታት
ድርጅቶች በኩል የሚታተሙ ሰነዶች፣ በኢትዮጵያ በመንግስት፣ መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማትና በአካል ጉዳተኛ ሰዎች ድርጅቶች በኩል
የሚነደፉ ፖሊሲዎች፣ መርሀ-ግብሮችና እንቅስቃሴዎች እንደዚሁም የክልላዊና ዓለምአቀፋዊ ድርጅቶች የሚመለከቱ ጠቃሚ ሰነዶች ያካትታል፡፡
ኢ.ሲ.ዲ.ዲ. አዲስ አበባ በሚገኘው
ጽ/ቤቱ አካል ጉዳተኝነትን የሚመለከቱ የተለያዩ የታተሙ ሰነዶች፣ የብሬይል ቅጅዎች፣ ሲዲዎችና እንዲሁም ሌሎች ጠቃሚ
ሰነዶችን አከማችቷል፡፡ ይህም ኢ.ሲ.ዲ.ዲ. አዲስ አበባ በሚገኘው ጽ/ቤቱ ሕብረተሰቡ በአጠቃለይ እንደዚሁም አካል ጉዳተኛ
ሰዎችና ቤተሰቦቸቸው፣ ተማሪዎች፣ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች፣ የፖርላማ አባላት፣ የልማትና ተራድኦ ተቋማት ተጠቃሚ
እንዲሆኑ ይሻል፡፡
የመረጃ አገልግሎት ማእከል ሰነዶችን መጠቀም የሚቻለው በኢ.ሲ.ዲ.ዲ. ጽ/ቤት ብቻ ሲሆን ተፈላጊ ሰነዶችን በቅጅ የመውሰድ አገልግሎትም ይሰጣል፡፡ የኢ.ሲ.ዲ.ዲ. ጽ/ቤት በሥራ ቀናት ከሰዓት በፊት ከ2፡00 - 6፡00 እና ከሰዓት በኃላ ከ7፡00 - 11፡00 ሰዓት ክፍት ነው፡፡
በተጨማሪም ኢ.ሲ.ዲ.ዲ. በኢትዮጵያ በአካል ጉዳተኝነት ዙርያ በድህረ -ገፅ የተደገፈ ኤለክትሮኒክ የመረጃ ማእከል አደራጅቷል፡፡ ይህ ኤለክትሮኒክ የመረጃ ማእከል የማህበራዊና ሠራተኞች ጉዳይ ሚኒስተር፣ የዩኒሴፍ ኢትዮጵያ አና የኢ.ሲ.ዲ.ዲ. የጋራ ፕሮጀክት ነው፡፡ ኢ.ሲ.ዲ.ዲ. የኤለክትሮኒክ መረጃ በሲዲ በመቅዳት ለመንግስት መሰሪያ ቤቶች መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች እና ለዩኒቨርስቲ ቤተ-መፃህፍት በየዓመቱ ለማሰራጨት አቅዷል፡፡