በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎች
ዲስክ ማለት ምንድነው? ዲስክ በኢንግሊዝኛው ፊደል “ዲስኤቢሊቲ ኢንፎርሜሽን ሰርቪስስ ሴንተር“
ከሚለው በምህፃረ-ቃል የተወሰደ ሲሆን በኢ.ሲ.ዲ.ዲ. በኩል በአካል ጉዳተኝነት ዙሪያ ለተጠቃሚዎች መረጃ የሚያቀርብ ማእከል
ነው፡፡ ዲስክ በኢትዮጵያ አካል ጉዳተኝነትና ልማትን፣ አካል ጉዳተኞችና ቤተሰቦቻቸው የሚመለከቱ አገልግሎቶች እና ምርቶች
እንዲሁም አካታች ልማትን እንዴት በተጨባጭ ማስፋፋት እንደሚቻል መረጃዎች ያቀርባል፡፡ ዲስክ በኢ.ሲ.ዲ.ዲ. ፅ/ቤቱ ካሰባሰባቸው
መረጃዎች መፅሃፎች፣የአማረኛና የኢንግሊዝኛ ብሬይል ፅሁፎ ቅጅዎች፣ ሲዲዎች እና በርካታ አካል ጉዳተኘነትን የሚመለከቱ ጠቃሚ
ሰነዶች ይገኙበታል፡፡
ዲስክ ምን ዓይነት መረጃዎችን አካቷል? ዲስክ ካሰባሰባቸው መረጃዎች ውስጥ በኣካል ጉዳተኘነትና በልማት ዙርያ በኢትዮጵያና
በዓለምአቀፍ ደረጃ የሚሰሩ ድርጅቶች፣ በኢትዮጵያ ለአካል ጉዳተኞች የሚሰጡ አገልግሎቶችና ምርቶች፣ እንደዚሁም ልማትን
የሚመለከቱ አጠቃላይ ርእሰ ጉዳዮች የያዙ ሰነዶችና መረጃዎች ይገኙበታል፡፡