ዜና እና አበይት ክንዋኔዎች
የኢ.ሲ.ዲ.ዲ. - አቢሊስ ፋውንዴሽን አጋርነት
ፊንላንድ በሚገኘው በአብሊስ ፋውንዴሽን እና በኢ.ሲ.ዲ.ዲ መካከል ያለው የአጋርነት ትብብር ለሁለት ዓመት ማለትም ከ2000-2001 ታድሷል፡፡ ስምምነቱ ኢ.ሲ.ዲ.ዲ በኢትዮጵያ የአቢሊስ ፋውንዴሽን ሕጋዊ ተወካይ መሆኑን ይገለጻል፡፡ በዚህ ስምምነት መሰረት ኢ.ሲ.ዲ.ዲ. የአካል ጉዳተኞች ማሕበራት የገቢ ማስገኛ፣ የሙያ ሥልጠና ወይም የአቅም ግንባታ ፕሮጀክቶች እንዲያቅዱ እና ለገንዘብ ዕርዳታ ወደ አቢሊስ ፋውንዴሽን እንዲቀርቡ ያደርጋል፡፡
የኢ.ሲ.ዲ.ዲ. ማሕበር ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ
የኢ.ሲ.ዲ.ዲ. ማሕበር ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ሚያዝያ 4 ቀን 2000 ዓ.ም. የተካሄደ ሲሆን በዚሁ ስብሰባ ላይ የቀድሞው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፓብሊክ
ፕሬዚዳንት ክቡር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በክብር እንግድነት ተገኝተዋል፡፡ በንግግራቸው ወቅት ዶ/ር ነጋሶ በኢትዮጵያ የፕሮቴስታንት የመጀመርያው ቄስ የነበሩት ዓይነስውር አባታቸው
ሕይወት ታሪክ ተናግረዋል፡፡
የተባበሩት መንግሥታት የአካል-ጉዳተኞች መብት ድንጋጌ
(ኮንቬንሽን)
የተባበሩት መንግሥታት የአካል-ጉዳተኞች መብት ድንጋጌ (ኮንቬንሽን)
ታኅሣሥ 1999 የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ አዲስ የሰብአዊ መብት ማስከበርያ ሰነድ ማዘጋጀቱ ይታወሳል። ይህም የአካል-ጉዳተኞቸች መብት ድንጋጌና እርሱን ማስፈጸሚያ ፕሮቶኮል የያዝ ነው። የኢትዮጵያ ፈዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፓብሊክ መንግሥትም ይህን ሰነድ እንደሚቀበለው መጋቢት 2000 ዓ.ም. ፈርሟል። ይህ ግን ተጨማሪውን “ፕሮቶኮል” አያካትትም። ይህም መንግሥት ሰነዱን በኢትዮጵያ እንዲፀድቅና ሕግ ሆኖ እንዲያገለግል ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል።
ይህ ድንጋጌ በዓለም አቀፍ ደረጃ 20 የተባበሩት መንግስታት አባል አገራት ካፀደቁት በኋላ ተግባራዊ ሆኗል። የኢትዮጵያ ማሕበራዊና ሠራተኛ ጉዳይ ሚኒስቴር ድንጋጌው በሚኒስትሮች ምክር ቤት ታይቶ እና ድጋፍ አግኝቶ በህዝብ ተወካዮች ምክር
ቤት እንዲፀድቅ አጥብቆ በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡
ኢ.ሲ.ዲ.ዲ - ላይት ፎር ዘ ወርልድ ፕሮጀክት
አውስትርያ የሚገኘውና በአካል ጉዳተኘነት ዙርያ በታዳጊ ሃገሮች የሚካሄዱ የልማት ፕሮጀክቶች በመደገፍ የሚታወቀው - ላይት ፎር ዘ ወርልድ በአዲስ አበባ ውስጥ አካል ጉዳተኘነትን በተመለከተ
ኢ.ሲ.ዲ.ዲ.ን የተደራሽነት ጥናት ለማካሄድ የሚያስችለው ደጋፍ አድርጎለታል፡፡
ጥናቱ የሚያተኩረው ሆቴሎችና እንግዳ ማረፍያ ቦታዎች፣ ቡና ቤቶችና ምግብ ቤቶች፣ ሲኒማና ቲያትር ማሳያ ቦታዎች፣ገበያ ማእከላት፣ ስፖርት ማዘውተርያ ስፍራዎች እንዲሁም ህዝባዊ የአገልግሎት መስጫ ስፍራዎች በሚመለከት ሲሆን ተደራሽነትን በሚመለከት ለአገር ውስጥ ተጠቃሚዎችና ለውጭ ሃገር እንግዶች ጠቃሚ የሆኑ መረጃዎች በሰነድ መልክ ለማዘጋጀት ታስቧል፡፡ የፕሮጀክቱ ሥራ በ2001 ዓ.ም. ይጀመራል፡፡